Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ግጭት በሰለማዊ መንገድ እንዲፈታ ኢትዮጵያ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች – ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ግጭት ሰለማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ41ኛው የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ዛሬ ጠዋት ጅቡቲ በመገኘት ተካፍለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ‘’ወንድሜ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ በሱዳን ጉዳይ ላይ የተካሄደውን 41ኛውን የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በማስተናገዳቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ’’ ብለዋል፡፡

አክለው እንዳሉትም ፥ ኢትዮጵያ በሱዳን ያለው ግጭት በሰላም እንዲቋጭ የሚደረገውን ጥረት በፅኑ ትደግፋለች፡፡

ኢትዮጵያ በኢጋድ የሚደረገውን የሰላም እና መረጋጋት ሂደት በንቃት ስትደግፍ መቆየቷን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩና የልኡካን ቡድኑ ተሳትፏቸውን አጠናቀው ዛሬ ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.