Fana: At a Speed of Life!

አይ ኤም ኤፍ ሀብታም የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝርን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ሀብታም የሆኑትን ዝርዝር አስነብቧል፡፡

በተለያዩ ተለዋዋጭ የኢኮኖሚ መመዘኛዎች ይህ ደረጃ ሊለወጥ እንደሚችል በዘገባው ተዳሷል፡፡

አይ ኤም ኤፍ ባወጣው ደረጃ በኢኮኖሚዋ በቀዳሚነት የምትጠቀሰው ከ200 ሚሊየን በላይ የህዝብ ብዛት ያላት ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ ናት፡፡

ናይጄሪያ በፈረንጆቹ 2022 አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርቷ 477ቢሊየን ዶላር ሲሆን ፥ በዚህ አያያዟ ረዘም ላለ ጊዜ የአፍሪካ የሀብት ቁንጮ ሀገር ሆና መቆየቷ አይቀርም ሲል አይ ኤም ኤፍ ገምቷል፡፡

በፈረንጆቹ 2028 አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርቷ 915ቢሊየን ዶላር እንደሚሆን ተቋሙ ግምቱን ያስቀመጠ ሲሆን ፥ ናይጄሪያ በነዳጅና በጋዝ ምርቷ ትታወቃለች፡፡

በቀጣይም ሀብታሟ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ሆና ተቀምጣለች፡፡ ደቡብ አፍሪካ በማዕድን ማውጣት ፣ ግብርና እና አገልግሎቷ ትጠቀሳለች፡፡

ግብጽ ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ አንጎላ፣ ኬኒያ ጋና እና ታንዛኒያ ደግሞ ከሶሥት እስከ ዘጠኝ ያሉ ደረጃዎች ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአይ ኤም ኤፍ ሪፖርት መሰረት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ፥ በዚህም በ10ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧም ነው የተገለጸው፡፡

ይህም ኢትዮጵያ የፈጣን እድገቷ ምክንያት በዋነኝነት ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ እና መሰረተ ልማት እንደሆነ ድርጅቱ አሳውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.