Fana: At a Speed of Life!

ከጥር ወር ጀምሮ የአበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ይደረጋል- ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶች ከጥር ወር 2016 ጀምሮ የአበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን አስታወቀ።

ለፓሪስ ኦሊምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶችም ከወዲሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ነው የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬከተር መኮንን ይደርሳል ያስታወቁት፡፡

በሌላ በኩል ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ በስምንት አትሌቶች ቅጣት መተላለፉ እና ተጨማሪ ሁለት አትሌቶች ላይ ደግሞ በጊዜያዊነት ታግደው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ቀደም ሲል ባለስልጣኑ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.