Fana: At a Speed of Life!

በትራንስፖርት ዘርፉ ያለውን ክፍተት በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ነው-ከንቲባ አዳነች

 

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በትራንስፖርት ዘርፉ ያለውን ክፍተት በዘላቂነት ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበበ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ::

 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማዘመን እና በዘርፉ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመቅረፍ ዘመናዊ የትራንስፖርት ስርዓት መዘርጋት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

 

ከንቲባዋ በውይይቱ ወቅት ÷ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በቅርበት እና በተናበበ መንገድ በመስራት በዘርፉ ያለውን ክፍተት በዘላቂነት ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል::

 

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ እና ዘመናዊ የከተማ ሎጂስቲክ ስርዓትን ለመዘርጋት ሚኒስቴሩ ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

 

ሚኒስቴሩ  ሁሉንም የባለድርሻ አካላት ያካተተ የሎጂስቲክ ካውንስል በማቋቋም ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት እየሰራ እንደሆነም መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.