Fana: At a Speed of Life!

አቶ አረጋ ከበደ በደብረብርሃን ከተማ የኢንዱስትሪ የሥራ እንቅስቃሴን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እና ሌሎች የመንግስት አመራሮች በደብረብርሃን ከተማ የኢንዱስትሪ የሥራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ጎብኝተዋል።
 
በጉብኝታቸውም የፌቤላ ኢንድስትሪያል የመኪና መገጣጠሚያን ተመልክተዋል።
 
ፋብሪካው በተደራጀ መንገድ ማምረት የጀመረ በመሆኑ ለሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ ትልቅ አበርክቶ ያለው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
 
ደብረብርሃን ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ በመሆኗ አልሚዎች ከተማው ለማዕከላዊ ገበያ ያለውን ቅርበትና የአካባቢውን እምቅ አቅም በመጠቀም በሌሎች ዘርፎች መዋዕለነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
 
የክልሉ መንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለሁሉም ነገር መሰረት የሆነው ሰላምን የመጠበቅ ስራም ከሁሉም እደሚጠበቅ አመላክተዋል።
 
በአበበ የሸዋልዑል
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.