Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ርእሰ መስተደድር አቶ ተመሰገን ጥሩነህን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ በኢኮኖሚ፣ መሠረተ ልማት ዘርፍ፣ በማህበራዊ ዘርፍ እና የፍትህ ተቋማት ሪፖረት ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በቀረበው ሪፓርት ፀጥታ በማስጠበቅ በኩል በተሰራ ስራ በሺህ የሚቆሩ ተፈናቃዩችን ወደቀያቸው መመለሳቸው በጥንካሬ ቀርቧል።

በሌላ በኩል የግብርና ምርጥ ዘርና የግብዓት አቅርቦት እጥረት፣ የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የሚሆን የተዘዋዋሪ ፈነድ ለማግኘት መቸግራቸው እና የንፅህ የመጠጥ ውሃ አቅረቦት እጥረት እንደችግር ተነስቷል።

በተመሣሣይ የጣና እምቦጭ አረም ለማስወገድና ለመከላከል የክልሉና የፌዴራል መንግስት የሰጡት ትኩረት አንስተኛ መሆኑ በውይይቱ ቀርቧል።

በተለይ የክልሉ መንግስት በጣና ጉዳይ መስራት ያለበትን ስራ እየሰራ አለመሆኑ ነው የተነሳው።

ከዚህ ባለፈ በፌደራል መንግስት የሚሰሩ የመንገድ፣ የመብራትና የመስኖ እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶች ያለመገምገም ችግሮች መኖራቸውም ተመልክቷል።

 

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.