Fana: At a Speed of Life!

በህንድ የሙቀት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የሙቀት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተሰምቷል።

የሙቀት መጠኑ በተለይም በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ከፍተኛ ሆኖ መመዝገቡም ነው የተነገረው።

መዲናዋ ደልሂን ጨምሮ በተለያዩ ግዛቶች የሙቀቱ መጠን ከ47 ነጥብ 6 እስከ 50 ዲግሪ ሴሊሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህን ተከትሎም ባለስልጣናት ነዋሪዎች በተቻለ መጠን ቤታቸው እንዳይቆዩ እያስጠነቀቁ ነው።

የሙቀት መጠኑ አሁን ላይ በሃገሪቱ የተስፋፋውን የአንበጣ መንጋ ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት መሆኑም ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ዓለም አቀፍ የጤና ፈተና ከሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተዳምሮ አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሯል ነው የተባለው።

የአየር ትንበያ ባለሙያዎችም ከሰሞኑ ህንድና ባንግላዴሽን የመታው አምፋን አውሎ ነፋስ ለሙቀት መጨመሩ ምክንያት ነው ብለዋል።

እስካሁን በከፍተኛ ሙቀቱ ሳቢያ በሰው ህይዎት ላይ ስለደረሰው ጉዳት ግን የተባለ ነገር የለም።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.