Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በልጧል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረጉ 5 ሺህ 34 የላብራቶሪ ምርመራዎች 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
 
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 61 ምንም ዓይነት የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ ቫይረሱ ከሚገኘበት ሰው ጋር የሚታወቅ ንክኪ የላቸውም።
 
ኮቪድ-19 የተገኘባቸው 71 ወንዶች እና 24 ሴቶች ሲሆን፥ የእድሜ ክልላቸውም ከ15 ዓመት እስከ 80 ዓመት ውስጥ የሚገኝ ነው።
 
ከዚህ ውስጥ 56 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 3 ሰዎች ከትግራይ፣ 5 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 22 ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 3 ሰዎች ከሀረሬ ክልል ፣ 2 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል እንዲሁም 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
 
30 ሰዎች የጉዞ ታሪክ ያላቸው እንዲሁም 4 ሰዎች ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሲሆኑ፥ 61 ደግሞ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ናቸው ተብሏል።
 
በተያያዘም በትናንትናው እለት 11 ሰዎች(2 ከትግራይ ክልል፣ 9 ከአፋር ክልል ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 208 ደርሷል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካሁን 106 ሺህ 615 ሰዎች የቫይረሱ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን÷ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 63 ደርሷል።

 

በአሁን ሰዓት በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 845 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ አምስቱ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.