Fana: At a Speed of Life!

በጋሞ ዞን በናዳና ጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደርች በሰፈራና ስግሰጋ ለማስፈር ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ እና ጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደርች በሰፈራና ስግሰጋ ለማስፈር ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መዘጋጀቱን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ገለፀ።

በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች በጎርፍ እና ናዳ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ በተደጋጋሚ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ ሰሞኑን በጣለው ዝናብ መብዛትም ተመሳሳይ ጉዳት ደርሷል።

ይህን አስመልክቶም የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች በጋጮ ባባ ወረዳ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደሮች በማጽናናት አካባቢውን ጎብኝተዋል።

የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በጋጮ ባባ ወረዳ በጎርፍና ናዳ የተጎዱ አካባባዎችን በጎበኙበት ወቅት በነዋሪዎች ላይ በደረሰው ያልታሰበ የሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በአስቸኳይ ከአካባቢው እንዲወጡ እና የዕለት እርዳታ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፥ በዘላቂነት ተፈጥሮን መጠበቅና በዞኑ ባሉ ሌሎች አመቺ ቦታዎች ላይ በሰፈራና በስግሰጋ ለማስፈር የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ለዚህ ስራ በአምስት ወረዳዎች ላይ በሰፈራና በስግስግ ለማስፈር 10 ሺህ ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ የመሬት ዲዛይን እየተሰራ መሆኑ ተጠቅሷል።

ዲዛይኑ ሲያልቅ የሰፋሪዎችን ቁጥር በመለየት የማስፈር ስራው ይሰራል ተብሏል።

በወረዳው ከጥር 21 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በተከሰተ ጎርፍ እና ናዳ 16 ሰዎች ሕወታቸውን ሲያጡ 112 አባወራዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ በአደጋው 8 ሺህ 687 ቤተሰቦች መፈናቀላቸውን ከጋሞ ዞን መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.