Fana: At a Speed of Life!

ያለማቋረጥ ከ227 ሰዓታት በላይ ምግብ ያዘጋጀችው ጋናዊት ሼፍ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋናዊቷ ሼፍ ፋይላቱ አብዱል ራዛክ ያለማቋረጥ ከ227 ሰዓታት በላይ ምግብ የማዘጋጀት ተግባር አከናውናለች።

ይህም ያለማቋረጥ ምግብ በማዘጋጀት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ሊያደርጋት እንደሚችል ተነግሯል።

ጋናዊቷ የምግብ ማብሰል ባለሙያዋ እንስት ለቀናት የቆየው የምግብ ማብሰል ቆይታዋ ፈታኝ ቢሆንም ለሀገሬ ጋና ስል ያደረኩት ነው ስትል ተናግራለች፡፡

በሀገሯ ባንዲራ ተጎናጽፋ ምግብ ስታበስል የነበረችው ሼፍ ፋይላቱ ምግቧን ለቀናት ቀጥ ብላ ስታበስል ቆይታ ስታጠናቅቅ በምግብ ቤቱ የነበሩ ሁሉ አሞካሽተዋታል፡፡

ይህን የምግብ ማብሰል ሂደት የሚያሳይ መረጃም ለጊነስ የዓለም አቀፍ ክብረወሰን መላኩም ነው የተጠቆመው፡፡

አሁን ላይ ረጅም ሰዓት የምግብ ማብሰል ሪከርዱ አላን ፊሸር በተባለ አየርላንዳዊ የተያዘ ሲሆን ፥ ሰዓቱም 119 ሰዓት ከ57 ደቂቃ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የምግብ ማብሰል ባለሙያዋ እንዳለችው፥ ማንኛውም ያሻሻልኩትን ሪከርድ ለመስበር ያሰበ ሰው አሰቸጋሪ ይሆንበታል ስትል ተናግራለች፡፡

ፖለቲከኞች፣ የጋና ምክትል ፕሬዚዳንት ማሃሙዱ ባውሚያን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ሰዎች እና የጋና ጦር ሰራዊት አባላት ሳይቀሩ በምግብ ማብሰል ሂደቱ ለባለሙያዋ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ሂልዳ ባሲ በናይጄሪያ ውስጥ በሼፍ ፊሸር ከመበልጧ በፊት ሪከርዱን መስበሯ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.