Fana: At a Speed of Life!

323 ኢትዮጵያዊያን በሁለተኛው ዙር  ከሊባኖስ ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 323 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በ2ኛው ዙር ዛሬ ከሊባኖስ ወደ አገራቸው  ተመለሱ ።

ኢትየጵያውያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴአታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የሴቶቸ፣ ህጸናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ፣ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ጉዳይ የኢትዮጵያ ተወካይ ማውሪን አቼንግ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አካላት ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ የሚመራ 11 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቋቁመውና በሰላም ሚኒስቴር ከሚመራው ግብረ ሃይል ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም ባለፈው ሃሙስ ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓ.ም 333 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሙሉ ወጪ በመሸፈን ከሊባኖስ እንዲመለሱ ማድረጉ የሚታወስ  ነው።

በዚህም የዛሬውን ጨምሮ በዚህ ሳምንት ከሊባኖስ የተመለሱ አጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 656 ደርሷል።

በቀጣይም በተለያዩ አገራት  በአስጨጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ትዮፕያውያንን  ወደ አገራቸው  ኢትዮጵያውያን  ለማስመለስ አስፈላጊው ክትትል  የሚደረግ መሆኑን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.