Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 109 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሶስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2 ሺህ 836 የላብራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
 
በዚህም በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 1ሺህ 172 ደርሷል።
 
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 99ኙ ከአዲስ አበባ ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል ፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል እና 3 ሰዎች ከሀረሪ ክልል ናቸው።
 
ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 209 ደርሷል።
 
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሶስት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል ፤ አንደኛዋ የ29 ዓመት በትግራይ ክልል የሰቲት ሁመራ ነዋሪ፣ ሁለተኛ የ75 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ እና ሶስተኛ የ55 ዓመት በደቡብ ክልል የከፋ ዞን ነዋሪ (በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የመጣ) ናቸው።
 
በመሆኑም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 11 ደርሷል፡፡
 
የመጀመሪያ ሁለቱ ግለሰቦች በሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ሶስተኛው ህይወቱ ያለፈና ለአስክሬን ምርመራ ወደ ሆስፒታል የመጣና በተደረገልት ምርምራ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ነው።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.