Fana: At a Speed of Life!

የአትክልት እና ፍራፍሬ ዋጋን በመጨመር በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትክልት ተራ ዋጋን መነሻ በማድረግ የአትክልት እና ፍራፍሬ ዋጋን በመጨመር በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የኮረና ቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ የንግዱን ማህበረሰብም ሆነ ሸማቹን በፍትሃዊ መንገድ ተጠቃሚ ለማድረግ እና የበሽታውን ተጋላጭነት ለመከላከል በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጿል፡፡

ነገር ግን በተለይ አንዳንድ በአትክልት እና ፍራፍሬ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ከአትክልት ተራ ዋጋ በላይ በተጋነነ ዋጋ በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ ቢሮው ባደረገው ክትትል እና ቁጥጥር ለማረጋገጥ ተችሏል ነው የተባለው፡፡

በዚህም ማንኛውም በዚህ ዘርፍ የተሰማራ ነጋዴ የአትክልት ተራ ዋጋን መነሻ በማድረግ በአማካኝ የሃበሻ ማንጎ 10 ብር ፣ የውጪ ገበያ የጥራት ደረጃን ያሟላ 20 ብር፣ አቮካዶ 10 ብር እንዲሁም ሙዝ ከ10 እስከ 12 ብር በመሸጥ ማስተካከያ እንዲያደረግ ቢሮው አሳስቧል፡፡

በተቀመጠው ማስተካከያ መሰረት ተግባራዊ በማያደርጉ ነጋዴዎች ላይም አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ቢሮው ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.