Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር 500 ሺህ ማስኮችና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለከተማ አስተዳደሩ አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር 500 ሺህ ማስኮችና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አበረከቱ።

አምባሳደሩ ከ6 የቻይና ተቋማት የተሰባሰቡ የአፍና አፍጫ መሸፈኛ ጭምብሎች (ማስኮችን) የተለያዩ ቁሳቁሶችን በዛሬው እለት ለምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስረክበዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ተቋማትም 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፥ 180 ሺህ ብር የሚገመት በእግር የሚሰራ እጅ መታጠቢያ ድጋፍም ተደርጓል።

ድጋፉን የተረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ የከተማ አስተዳደሩ አስቸጋሪ ወቅቶች ቢከሰቱ በሚል በየአካባቢው ነዋሪዎች የተዋቀረ የብሎክ አደረጃጀት በመፍጠር እንዲሁም የምግብ ባንክ በማዘጋጀት ዝግጅት እንዳደረገ ተናግረዋል።

ለዚህም ከተለያዩ ዜጎች የሚደረጉ ያልተቋረጡ ድጋፎች ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ህብረተሰቡ በቻለው መልኩ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በድጋፍ የተገኙት ማስኮች ለመንግሥት ሠራተኞች፣ ለጤና ባለሙያዎች እና ለፖሊሶች የሚከፋፈሉ መሆኑንም የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.