Fana: At a Speed of Life!

ከ23 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 23 ነጥብ 45 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ፡፡

የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የግማሽ አመት ዕቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ሲሆን÷የስድስት ወራት የኦፕሬሽን፣ የፋይናንሺያል እና የካፒታል ፕሮጀክት ሥራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በግማሽ ዓመቱ አጠቃላይ የድርጅቱን የኦፕሬሽን አገልግሎት መጠን 2 ሚሊየን 544 ሺህ 810 ቶን ለማድረስ ታቅዶ ወደ 3 ሚሊየን 674 ሺህ 242 ቶን ማድረስ እንደተቻለም ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በፋይናንሺያል አፈፃፀም 23 ነጥብ 45 ቢሊየን ብር ገቢ እና ከታክስ በፊት 3 ነጥብ 26 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘት ተችሏል ተብሏል፡፡

ግምገማው ነገም የሚቀጥል ሲሆን÷ የቀጣይ ስራዎች አተገባበር ላይም ውይይት የሚደረግ መሆኑን የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.