Fana: At a Speed of Life!

ከማዕድን ወጪ ንግድ 142 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ወጪ ንግድ 142 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ገቢው ለውጪ ገበያ ከቀረቡ የወርቅ፣ ታንታለም፣ ሊቲየም ኦር፣ ጌጣጌጥና የኢንዱስትሪ ማዕድናት የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሕገ-ወጥ የማዕድን ምርትና ግብይትን ለመቅረፍ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ እንደሚከናወን መጠቆሙንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.