Fana: At a Speed of Life!

ናንጎሎ ምቡምባ የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሃጌ ጌንጎብ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ የሀገሪቱ የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ናንጎሎ ምቡምባ አዲሱ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
 
ምቡምባ በዋና ከተማዋ ዊንድሆክ በትናንትናው ዕለት ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን÷ ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋህ ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል፡፡
 
ምቡምባ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም በቀደሙ መሪዎች በተጣለ መሰረት ላይ መገንባታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
 
መስራቹ አባት በመባል በሚታወቁት ሳም ሻፊሹና ኑጆማ (ዶ/ር)፣ በቀድሞው ፕሬዚደንት ሂፊኬፑንዬ ፖሃምባ (ዶ/ር) እና በተወዳጁ ፕሬዚዳንታችን ሃጌ ጌንጎብ (ዶ/ር) በተጣሉት ግሩም መሰረቶች ላይ ሀገሪቱን የመገንባቱን ስራ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
 
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት የ82 ዓመቱ ጌንጎብ ለካንሰር ህክምና ሆስፒታል ከገቡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ትናንት ህይወታቸው ማለፉ መገለጹ ይታወቃል።
 
ጌንጎብ ከቀናት በፊት ለካንሰር ህክምና ሆስፒታል የገቡ ቢሆንም ህይወታቸውን ማትረፍ ሳይቻል መቅረቱ ተገልጿል።
 
በሀገሪቱ ህግ መሰረትም ምቡምባ በጌንጎብ ምትክ የፕሬዚዳንትነት ቦታውን እንዲረከቡ መደረጉን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስታወቁን ዢንዋ ዘግቧል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.