Fana: At a Speed of Life!

2 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገበ ኩባንያ ወደ ስራ ሊገባ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 2 ቢሊየን ብር ኢንቨስት የተደረገበት ገሊላ የቆዳ ጫማና ሶል ማምረቻ ኩባንያ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ÷ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ስራ እስኪጀምር ድረስ የኮርፖሬሽኑ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በፓርኩ 7 ሺህ ስኩዌር ሜትር መሬት ላይ የለማው ገሊላ ማኑፋክቸሪንግ ኮርፖሬሽን ለሀገር በቀል ባለሀብቶችና ኩባንያዎች የተሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ማኑፋክቸሪንጉ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የለማ መሬት በመውሰድ የቆዳ ጫማዎችን እና ሶሎችን ለማምረት ማምረቻ ገንብቶ እንዳጠናቀቀ ተገልጿል፡፡

ማምረቻ ማሽኖችንም የመገጣጠም እና የመጨረሻ ጥቃቅን ስራዎችን የማጠናቀቅ ስራ ብቻ እንደሚቀረው የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኩባንያው 2 ቢሊየን ብር ያህል ኢንቨስት እንዳደረገ እና ከ2 ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል እንደሚፈጥር ተጠቅሷል፡፡

ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ምርቶቹን ለጣሊያን፣ ለቱርክና ለሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ገበያ እንደሚያቀርብ ተመላክቷል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.