Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ባለፉት 6 ወራት ከ170 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መሰጠቱን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ከ170 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ከግል ሴክተሮችና ለባንኮች መሰጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ÷ በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራት ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ፣ ዓለም አቀፋዊ ግጭቶች፣ የውስጥ ችግሮች እና የውጭ ጫናዎች በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ ጫና ማሳደሩንም አብራርተዋል፡፡

በእነዚህ ድምር ምክንያቶች የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራትን መጠገን አልቻልንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የማክሮ ፋይናንሻል መዛባትን በሚመለከት የተሠራው ፊፎርም በብዙ ማሳያ ከፍተኛ መሻሻሎች ታይቶበታል ብለዋል፡፡

የብር ኖት ከመቀየር ጀምሮ ሲሠራ የነበረው ሪፎርም በተወሰነ ደረጃ መሻሻል እንዲታይ ማድረጉን ጠቅሰው÷ በቀጣይ መታየት ያለባቸውና ቀሪ ሥራ የሚፈልጉ ጉዳዮች እንዳሉም አመላክተዋል፡፡

የፊሲካል ፖሊሲ አቅጣጫዎችና ሥራዎች አሁን ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥሉት መንግሥታትም ጭምር ፋይዳ ሊያመጡ የሚችሉ ስብራቶች ተጠግነውበታል ነው ያሉት፡፡

በየሻምበል ምሕረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.