Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቡና ዐውደ ርዕይ በቴሌአቪቭ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በእስራኤል ቴሌአቪቭ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ የኢትዮጵያ ቡና ዐውደ ርዕይ አካሄደ።

በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ረታ ዓለሙ የመርሀ ግብሩ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን ቡና ማስተዋወቅ መሆኑን አስታውቀዋል።

መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን ባህል ምግብ፣ በማስተዋወቅ ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ባህል ምግብ ቤቶች እውቅና መስጠት እና ማበረታታት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ምግብ ዲፕሎማሲ እና ቡና ኤግዚቢሽን መርሀ ግብሩ ከዚህ በፊት በቴል አቪቭ መካሄዱ የሚታወስ ነው።

ዓላማውም ለኢትዮጵያ የቡና ምርት በእስራኤል ገበያ ማጠናከር፣ የኢትዮጵያን ምግብ በማስተዋወቅ ገጽታ መገንባት እንዲሁም የቱሪስት ፍሰትን መጨመር መሆኑን አምባሳደር ረታ ዓለሙ ገልጸዋል።

በዚህ ወቅት የኢትዮጵያን ቡና አይነቶች እና የኢትዮጵያ የቡና አፈላል ሥርዓት በሚመለከት በዲፕሎማቶች ገለፃ ማቅረባቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የኢየሩሳሌም ከተማ ከንቲባ ተወካይ፣ የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ አባላት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤቶች፣ የኢትዮጵያን ቡና አስመጪዎች፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር አባላት፣ጋዜጠኞች፣ተጋባዥ እንግዶች፣ በእስራኤል የሚገኙ የሚዲያ አባላት ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.