Fana: At a Speed of Life!

ሃማስ ለቀረበው የ135 ቀናት የተኩስ አቁም ዕቅድ ምላሽ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃማስ የፍልስጤም እስረኞችን በታጋቾች መለዋወጥና ጋዛን መልሶ መገንባትን ጨምሮ ተያያዥ ጥያቄዎች እንዲፈቱ በመዘርዘር እስራኤል ላቀረበችው የተኩስ አቁም ዕቅድ ምላሽ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
 
ታጣቂ ቡድኑ ከሶስት የ45 ቀናት የእርቅ ሂደት በኋላ የእስራኤል ጦር ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ እና ጦርነቱ እንዲያበቃም ፍለጎት እንዳለው ገልጿል።
 
ይሁንና ጥያቄው በጋዛ ጠቅላላ ድል እንዲደረግ ጥሪ ባቀረቡት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በኩል ተቀባይነት ላይኖረው እንደሚችል ተመላክቷል፡፡
 
ዝርዝር ጉዳዩ በይፋ ባይገለፅም የሃማስ ምላሽ በእስራኤል እና በአሜሪካ ለሚደገፈው እና በኳታር እና በግብፅ አሸማጋይነት ለቀረበው የተኩስ አቁም ዕቅድ የቀረበ የአፀፋ ምላሽ መሆኑ ተጠቁሟል።
 
ሃማስ ባቀረበው ረቂቅ ሰነድ መሰረትም÷ በመጀመሪያው ምዕራፍ የ45 ቀናት የተኩስ አቁም ሁሉም እስራኤላውያን ሴቶች፣ ከ19 ዓመት በታች የሆኑ ወንዶች፣ አረጋውያንና ታማሚ ታጋቾች በእስራኤል እስር ቤቶች ባሉ ፍልስጤማውያን ሴቶችና ህፃናት ልውውጥ ይደረጋል፡፡
የእስራኤል ወታደሮች ህዝብ ከሚበዛባቸው የጋዛ አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡና የሆስፒታሎች እና የስደተኛ ካምፖች መልሶ ግንባታ ይጀመራል፡፡
 
በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ የተቀሩት ወንድ እስራኤላውያን ታጋቾች በተቀሩት ፍልስጤማውያን እስረኞች ልውውጥ የሚደረግበት እና የእስራኤል ወታደሮች ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለቀው የሚወጡበት ይሆናል፡፡
 
ሦስተኛው እና የመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ ሁለቱም ወገኖች የሟቾችን አስከሬን የሚለዋወጡበት እንደሚሆን ተጠቅሷል።
 
ስምምነቱ ለጋዛ የምግብ እና ሌሎች ተጨማሪ ዕርዳታዎችን ለማድረስ የሚያስችል ሲሆን በ135 ቀናት ማብቂያ ላይ ጦርነቱን በማቆም ድርድሩ እንደሚጠናቀቅ ሃማስ በምላሹ ማካተቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
ይሁንና ዕቅዱ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በኩል “ከልኩ ያለፈ” የሚል ምላሽ እንደተሰጠውም ነው የተገለጸው፡፡
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.