Fana: At a Speed of Life!

የብዝሃ ሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያ የውጪ ምንዛሬ ማስገኘት የሚያስችለውን ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የብዝሃ ሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያ የውጪ ምንዛሬ ማስገኘት የሚያስችለውን ሥራ መጀመሩ ተገለጸ፡፡

በ2013 ዓ.ም የብዝሃ ሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያ በመገንባት ወደ ስራ መገባቱን የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ አስታውሰዋል፡፡

ጣቢያው ከሳተላይቶች ጥራት ያለው መረጃ ከመቀበል ባሻገር የገበያ እድሎችን ለመፍጠር ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመስራት የጣቢያውን አገልግሎት ለሚፈልጉ ድርጅቶችና ሀገራት ሳተላይቶቻቸው በሚያልፉበት ብዛት ወይም በተጠቀሙበት ደቂቃ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

በዚህ የመሬት መረጃ መቀበያ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ሥራም ከ10 በላይ ሳተላይቶችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በማድረግ የውጪ ምንዛሬ ማስገኘት የሚያስችል አቅም መገንባት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

እንጦጦ ያለው የብዝሃ ሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያ ከ11 ሳተላይቶች ተልዕኮ መቀበል፣ መረጃ መሰብሰብ እና ወደ ተፈለገው የአገልግሎት አድራሻ ማገናኘት የሚያስችሉ ሥራዎች ተጠናቀው ወደ የመረጃ መቀበያ ጣቢያ ያልተቋረጠ አገልግሎት መስጠት ተግባር ተገብቷል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.