Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ከግሎባል ፈንድ ጋር የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋት ያለመ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ከግሎባል ፈንድ ልኡካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በግሎባል ፈንድ ቀጣይ የሦስት ዓመት ፈንድ ዙሪያ እንደ ሃገር በቀረበው ጥያቄ መሰረት ግራንት ማጠናቀቂያ ላይ ውይይት ለማድረግ ከመጣው ልዑካን ቡድን ጋር ነው ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የተወያዩት፡፡

ቡድኑ በጤና ሚኒስቴር ግሎባል ፈንድ የተሰሩ ፕሮጀከቶች ያሉበትን ደረጀ የጎበኙ ሲሆን ÷ የጉብኝታቸው ሪፖርትም ቀርቧል፡፡

ልኡካኑ ባቀረበው ሪፖርት በጤና ሚኒስቴር እየተተገበሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በተገቢው መልኩ እየተፈጸሙ መሆኑን መመልከታቸውንም ነው ያነሱት፡፡

በተጨማሪም በግሎባል ፈንድ የአደጋ መከላከል ቡድን በአርባምንጭ የመስክ ጉብኝት በማድረግ በጤና ተቋማት እንዲሁም የግብዓት ስርጭትን በተመለከተ በህብረተሰቡ መካከል ያለውን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋት ምልከታ አድርገው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡

ከጉብኝቱ መልስ የልኡካን ቡድኑ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የድጋፍ መጠይቅ ገምግመው ግብረመልስ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡

ቡድኑ በገመገመው መሰረት በቲቢ፣ በወባ፣ በኤች አይ ቪ እንዲሁም በአጠቃላይ የጤና ዘርፍ ለሚያግዝ የተጠየቀው ድጋፍ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሻሻሉ የተጠየቁት ነጥቦች ተስተካክለው እንዲቀርቡ በውይይቱ መግባባት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.