Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥን ከሥራ አሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 01፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ የሀገሪቱን ጦር ዋና አዛዥ ጄነራል ቫለሪ ዛሉዥኒን ከሥራ ማሰናበታቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ ዋና አዛዡን ከሥራ ያሳናበቱት በመካከላቸው የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ተሰናባቹን ዋና አዛዥ በመተካትም በዘርፉ በርካታ ልምድ ያላቸው ጄነራል ኦሌክሳንደር ሰሪስኪ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ይህም ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባችበት ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ ጦር የተደረገ ከፍተኛ የአመራር ለውጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጄነራል ቫለሪ ዛሉዢኒ በዩክሬን ወታደሮች እና ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው እና በሀገሪቱ ሕዝብ እንደ ብሔራዊ ጀግና የሚቆጠሩ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አውስቷል፡፡

ጀነራሉ በዩክሬን ሕዝብ ዘንድ ያላቸው ቅቡልነትም ከፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ የተሻለ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.