Fana: At a Speed of Life!

በመጽሐፍ ህትመት ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ፋብሪካ ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 01፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጽሐፍ ህትመት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ፋብሪካ ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት መደረጉን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ያጋጠመው የመጽሐፍ እጥረት ከህትመት ጋር ተያይዞ የሚጠይቀው ወጪ እና የሚታተምበት ቦታ ከሀገር ውጪ በመሆኑ የተከሰተ ነው።

በመሆኑም ስምምነቱ የአዲሱ ትምህርት ስርዓት የመማሪያ መጽሐፍ እጥረትን ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ የሚያስችል እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር የታተመው የመማሪያ መጽሐፍ መሰራጨቱን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በዚህም 1 ለ 5 የነበረውን የመጽሐፍ ጥምርታ በተወሰኑ አካባቢዎች 1 ለ 2 ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ለሁለተኛ ዙር እየታተመ ያለው መጽሐፍ ሲጠናቀቅበሁሉም አካባቢዎች አንድ መጽሐፍ ለሁለት ተማሪዎች እንዲዳረስ ይደረጋልም ብለዋል።

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.