Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑል እና ማንቼስተር ሲቲ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ሊቨርፑል እና ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ሊቨርፑል በርንለይን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ማጠናከር ችሏል፡፡

የሊቭርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ጆታ፣ ዲያዝ እና ኑኔዝ ሲያስቆጥሩ÷ የበርንለይን ብቸኛ ግብ ደግሞ ኦሼ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ማንቼስተር ሲቲ ኤቨርተንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ÷የማሸነፊያ ግቦችንም ኧርሊንግ ሃላንድ አስቆጥሯል፡፡

ቶተንሃም ደግሞ ብራይተንን 2 ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በሌላ በኩል ፉልሃም ቦርን ማውዝን ፣ ሼፍልድ ዩናይትድ ሉተንን በተመሳሳይ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ ብሬንት ፎርድ ደግሞ ወልቭስን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.