Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጎዴ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ሙስጠፌ መሐመድ የተመራ ልዑክ ሸበሌ ዞን ጎዴ ከተማ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ አቶ ሙስጠፌ መሐመድን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰውን እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ነው፡፡

ልዑኩ ጎዴ ከተማ ኡጋዝ ሚራድ ሌይሊ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም አቀባበል እንደተደረገለት ጠቅሶ የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.