Fana: At a Speed of Life!

“በጋዛ ያለውን ጦርነት ማስቆም የሚቻለው በፖለቲካዊ መንገድ ነው” – ኢራን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋዛ ያለውን ጦርነት ማስቆም የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ፖለቲካዊ መፍትሔ መሆኑን ኢራን ገለጸች፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂን በሊባኖስ ባደረጉት የአንድ ቀን ጉብኝት ከሊባኖሱ አቻቸው አብደላ ቡ ሀቢብ ጋር የቀጣናውን ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክተው የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም “የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ጨምሮ እስራኤል በሃማስ ላይ እየወሰደች ባለው ወታደራዊ እርምጃ ዙሪያ ኢራን ከአሜሪካ ጋር መልዕክቶች መለዋወጧ” ተነስቷል፡፡

በወቅቱም ሂዝቦላህ በእስራኤል-ሃማስ ጦርነት ላይ በስፋት እንዳይሳተፍ ቴህራን እንድትጠይቅላት አሜሪካ ማንሳቷን የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጸዋል።

ሃማስን ለመደገፍ በሊባኖስና እስራኤል ድንበር ከሚገኙት የእስራኤል ጦር ጋር እየተዋጋ ያለው ሂዝቦላህ÷ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጦርነት ከከፈተች እስከመጨረሻው ለመታገል ቃል መግባቱንም አስታውሰዋል፡፡

በአሜሪካ ወታደሮች ላይ በዮርዳኖስ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ዋሽንግተን በዚህ ወር መጀመሪያ በኢራቅ፣ ሶሪያና የመን በሚገኙ ከኢራን ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው ቡድኖች ላይ ጥቃት መሠንዘሯ ይታወሳል፡፡

ሚኒስትሮቹም በመግለጫቸው÷  እስራኤል በሊባኖስ ላይ ማንኛውንም እርምጃ እንዳትወስድ ማስጠንቀቃቸውን ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል፡፡

ኢራን እና ሊባኖስ ጦርነት መፍትሄ  ነው ብለው እንደማያምኑና ጦርነት እንዲስፋፋ በፍጹም ፍላጎት እንደሌላቸውም ነው በመጋራ መግለጫው የተገለጸው፡፡

ቴህራን ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር በጋዛ ባለው ጦርነት ዙሪያ ፖለቲካዊ መፍትሔ ማምጣት በሚቻልበት አግባብ ላይ እየተነጋገረች መሆኗም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.