Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ የሚኒስትሮች ኮሚሽን የጋራ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሦስተኛው የኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ስብሰባም÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተጠቅሷል፡፡

በተለያዩ ዘርፎች አዳዲስ የትብብር መንገዶች እንደሚዳሰሱ መገለጹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የፊታችን ማክሰኞ የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሚመሩት የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ላይም÷ አስር የሚጠጉ የመግባቢያ ሠነዶች በተለያዩ ሴክተሮች ኃላፊዎች እንደሚፈረሙ ይጠበቃል፡፡

ስብሰባው ሲጠናቀቅምበ ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት በማጠናከር በጋራ ለመስራት አዲስ ቃል እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.