Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን መረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን መረቁ፡፡

ከምረቃው በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ከዓድዋ ድል መታሰቢያው ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከመሬት በታች ሁለት ደረጃዎች እንዲሁም ከመሬት በላይ አምስት ወለሎች አሉት፡፡

የምሥራቅ ጀግኖች፣ የምዕራብ ጀግኖች፣ የሰሜን ጀግኖች፣ የደቡብ ጀግኖች፣ የፈረሰኞች፣ የአርበኞች እና የፓንአፍሪካኒዝም የተሰኙ በሮችም አሉት፡፡

እንዲሁም የአፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ፣ የ12ቱን የጦር መሪዎች ፣ በጦርነቱ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ፈረሶች መታሰቢያ ሐውልቶችና የጥበብ ሥራዎችም አሉ፡፡

ነጋሪትን ጨምሮ የኢትዮጵያውያን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና በቅርቡ ወደ ሀገር የገባችው ፀሐይ አውሮፕላን በዓድዋ ድል መታሰቢያው ይገኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.