ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ ሌይሊ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ነገ ይመረቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የሚገኘው ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ ሌይሊ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ነገ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተመላከተ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እና ሌሎች የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች የጎዴ ኡጋዝ ሚራድ ሌይሊ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናልን ጎብኝተዋል፡፡
ግንባታው የተጠናቀቀው ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ ሌይሊ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናልም ነገ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡