Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያን መረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ አዲስ የተገነባውን ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፡፡

አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

አውሮፕላን ማረፊያው ምቹ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ግንባታውን ያከናወነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

አውሮፕላን ማረፊያው በአንድ ጊዜ አራት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖችን ማስናገድ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

የተርሚል ግንባታው ሦስት ዓመት የፈጀ ሲሆን÷ የተሳፋሪዎችን ምቾት ለመጠበቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀ ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.