Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከቻይና የሚደረጉ የመንገደኞች አውሮፕላን በረራዎች ላይ እገዳ ጣለች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ ከቻይና የሚደረጉ የመንገደኞች አውሮፕላን በረራዎች ላይ እገዳ መጣሏ ተሰምቷል።

ከቻይና ወደ አሜሪካ የሚደረጉ የመንገደኞች አውሮፕላን በረራዎች ላይ የተጣለው እገዳ ከሰኔ 9 ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ የሚደረግ መሆኑም ነው የታወቀው።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ቢሮ እንዳስታወቀው፥ እገዳው የተላለፈው ቤጂንግ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ከተቆጣጠረች በኋላ የአሜሪካ አውሮፕላኖች ወደ ሀገሪቱ እንዲበሩ ፍቃደኛ ላለመሆኗ ቅጣት ነው።

እንደ ትራንስፖርት ቢሮው ትእዛዝ እገዳው ኤር ቻይና፣ ቻይና ኢስተርን ኤር ላይን፣ ቻይና ሳውዘርን ኤር ላይን እና ሀይናን ኤር ላይን በተባሉ አራት የቻይና አውሮፕላኖች ላይ ተፈፃሚ የሚደረግ ነው።

ሆኖም ግን የመንገደኞች አውሮፕላን እገዳው ተፈፃሚ ለመሆን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ይሁንታ ካገኘ ብቻ ነው እየተባለ ነው።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይናን በተደጋጋሚ ፍትሃዊ ባልሆነ የንግድ ስርዓት እንዲሁም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አያያዝ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ሲወቅሱ እንደነበረም አይዘነጋም።

በአሜሪካዋ ዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ የበረራ እገዳው ላይ እስካሁን አስተያየት ከመስጠት መቆጠቡም ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ bbc.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.