Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሰላምና ልማት ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ዛሬ ማለዳ ባሕር ዳር ከተማ ገብቷል፡፡

እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄዱ ሕዝባዊ ውይይቶች የሕዝቡ ፍላጎት ሰላም እና ልማት መሆኑ ጎልቶ መውጣቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

የአማራ ክልልም ሰላምን ከማጽናትና ልማትን ከማስቀጠል አንጻር ያሉትን ፀጋዎች ለይቶ በብቃት መሥራት፣ የአመራር አንድነትን ማስፈን፣ ሰላምን ለማጽናት በቁርጠኝነት መታገልና የተሟላ የሰላም ባለቤት መሆን ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

በውይይቱ ላይ በክልሉ ያሉትን ፀጋዎች እንዴት ማልማት እንደሚቻል፣ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ምን ሊሠራ እንደሚገባ፣ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ተግዳሮቶችን እንዴት መፍታት ይቻላል በሚሉ ጉዳዮች ምክክሩ እየተካሄደ ነው፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.