Fana: At a Speed of Life!

የብሪክስ ሀገራት 45 ትሪሊየን ዶላር ኢንቨስት ሊደረግ የሚችል ሃብት እንዳላቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪክስ አባል ሀገራት 45 ትሪሊየን ዶላር ኢንቨስት ሊደረግ የሚችል ሃብት እንዳላቸው የሄንሌይ እና ፓርትነርስ የብሪክስ የሃብት ሪፖርት አመላከተ፡፡

ቀደም ሲል ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካና ብራዚል አቅፎ የነበረው ብሪክስ ፥ በአሁኑ ወቅት ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኢራን፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በመቀላቀል ቡድኑ መስፋፋቱ ተጠቁሟል።

በሪፖርቱ መሰረት አሥሩ ሀገራት በአሁኑ ወቅት 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ግለሰቦች ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት ያደረጉ ግለሰቦች እንዳሏቸው ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም ከ4 ሺህ 700 በላይ ግለሰቦች ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት ያደረጉ ሲሆኑ ፥ ከ500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቢሊየነሮች ናቸው ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት 45 በመቶውን የዓለም ሕዝብ የሚያጠቃልለው ህብረቱ፥ 36 በመቶው የሚሆነውን የዓለም አቀፍ የሀገር ውስጥ ምርት እንደሚይዝም ተገልጿል፡፡

ይህም ከቡድን-7 ሀገራት ጋር ሲነጻጸር በ30 በመቶ ድርሻ የሚልቅ መሆኑ ነው የተመላከተው።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ሳዑዲ ዓረቢያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የግል ሃብት እድገት ማሳየታቸው በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ሚሊየነሮች ቁጥር በ30 በመቶ፣ ሳዑዲ ዓረብያ 35 በመቶ እንዲሁም የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በ77 በመቶ መጨመሩ ተጠቅሷል፡፡

ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በአሁኑ ወቅት በህብረቱ በሚሊየነሮች ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ቻይና 862 ሺህ 400 ሚሊየነሮች ያሏት ሲሆን ፥ ሕንድ 326 ሺህ 400 ሚሊየነሮች አሏት።

በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ቻይና 85 በመቶ እና ሕንድ 110 በመቶ በሚሊየነሮች ጠንካራ እድገት እንደሚያስመዘግቡ መገመቱንም አርቲ ዘግቧል።

#Ethiopia #BRICS

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.