Fana: At a Speed of Life!

በ250 ሚሊየን ብር የተገነባው የግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ በ250 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ፋብሪካ ተመርቋል።

ፋብሪካው በሰዓት ከ220 ቶን በላይ የግንባታ ግብዓቶችን የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡

የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሌሎች ባለሀብቶችም በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው፤ አሥተዳደሩም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደርግ አስታውቀዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው ፋብሪካም በሥራ ዕድል ፈጠራ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ማለታቸውን የአሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ያሲን መሐመድ በበኩላቸው÷ ድርጅቱ ከድሬዳዋ አልፎ የአጎራባች ከተሞችና ክልሎችን የግንባታ ግብዓት ፍላጎት ማሟላት ይችላል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.