Fana: At a Speed of Life!

የማህበረሰብ ስርዓተ ምግብን ለማሻሻል የ70 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ያለውን የማህበረሰብ ስርዓተ ምግብ ለማሻሻል የ70 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት በጤና ሚኒስቴር እና በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) መካከል ስምምነት ተፈረመ።

የፕሮጀክት ስምምነቱ በኢትዮጵያ የሴቶች፣ የህፃናት እና የታዳጊ ሴቶችን ስርዓተ ምግብ ለማሻሻል የሚውል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመከላከል አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ በኢትዮጵያ ለአደጋ ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የሰብዓዊ ድጋፎችን ለማቅረብ የሚውል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የማህበረሰብ አቀፍ ስነ-ምግብ ስርዓት ፕሮጄክቱ በኢትዮጵያ ስምንት ክልሎች እና እንድ የከተማ አስተዳር ውስጥ በሚገኙ 155 ወረዳዎች የሚተገበር መሆኑን ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.