Fana: At a Speed of Life!

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ከነተጠርጣሪዎቹ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዳማ፣ ወለንጭቲ፣ መተሃራ እስከ ቦርደዴ ድረስ የተዘረጋ የህገወጥ መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ቡድን በህገ-ወጥ መንገድ ሊያሻግሩት የነበረ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ተያዘ፡፡

ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ከነተጠርጣሪዎቹ የተያዘው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ክፍለጦር ባደረገው ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተጠርጣሪዎች ክላሽ፣ ቦምብና ከ9 ሺህ 600 በላይ ጥይቶች እንዲሁም የመሳሪያ ግዥ ይፈፀምበት የነበረ 600 ሺህ ብር መያዙን የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ገልፀዋል፡፡

ለፀረ-ሰላም ሃይሎች የሚደርሰውንና ለአካባቢው ብሎም እንደ ሀገር የሰላም ጠንቅ የሆነውን ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ከምንጩ ለማድረቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

በዚህም ህገ-ወጥ ዝውውሩ እጅግ ውስብስብና የተደራጀ መሆኑን መገለጹን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ ለጊዜያዊ ጥቅሞች ሲባል ዘላቂ ሰላሙን የሚያናጋ ህገ-ወጥ የመሳሪያ ዝውውር በአካባቢው እንዳይፈፀም የማድረግ ዜግነታዊ ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በመተባበር የተጀመረውን ኦፕሬሽን እንዲያግዝ ተጠይቋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.