Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ማክሮን በዩክሬን የሚያደርጉትን ጉብኝት መሰረዛቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በደህንነት ጉዳዮች ምክንያት በዩክሬን የሚያደርጉትን ጉብኝት መሰረዛቸው ተሰምቷል፡፡
 
የፕሬዚዳንት ማክሮን የዩክሬን ጉብኝት በፈረንጆቹ ከፊታችን የካቲት 13 እስከ 14 ቀን ታቅዶ እንደነበር ተገልጿል፡፡
 
በዚህም ማክሮን የዩክሬን ትልቁን የጥቁር ባሕር ወደብ ኦዴሳንና ኪየቭን ይጎበኛሉ ተብሎ መርሐ ግብር ተይዞ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
 
ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንቱ አሁን ላይ በቀጣናው ባለው የደህንነት ስጋት ሳቢያ ጉብኝታቸውን መሰረዛቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
የፈረንሳይ መንግሥት ጉዳዩን አስመልክቶ የሰጠው ምላሽ አለመኖሩንም አር ቲ በዘገባው አስፍሯል፡፡
 
የውጭ ሀገራት መሪዎች ለጉብኝት ወደ ዩክሬን የሚያቀኑበት ትክክለኛ ቀን አስቀድሞ እንደማይገለጽ ተመላክቷል፡፡
 
ማክሮን ለመጨረሻ ጊዜ ኪየቭን የጎበኙት ሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ከአራት ወራት በኋላ በፈረንጆቹ ሰኔ ወር 2022 ላይ እንደነበር ይታወሳል።
 
አዲሱ የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባሳለፍነው ጥር ወር ከፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ ጋር በኪየቭ ተገናኝተው ፓሪስ ተጨማሪ ድጋፍ እንደምትሰጥ ቃል መግባታቸው ተጠቁሟል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.