Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚዎች ም/ቤት ስብሰባ ረቡዕ እና ሃሙስ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በመጪው ረቡዕ እና ሃሙስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
 
በአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ላይም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡
 
በጉባዔው ሀገራት ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ እና እሑድ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.