Fana: At a Speed of Life!

የጣና ሀይቅ እምቦጭ አረምን መከላከልና ማስወገድ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን እምቦጭ አረም ለመከላከል እና ለማስወገድ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በባህርዳር ከተማ ውይይትተካሄደ።

በውይይቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሰት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች እና ምሁራን ተገኝተዋል።

በውይይቱ የጣና ሀይቅ እና የሌሎች ውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አያሌው ወንዴ፥ አረሙን በመከላከል እና በማስወገድ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት አቅረበዋል።

የጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተው የእምቦጭ አረም በ7 ወረዳዎች፣ 30 ቀበሌዎች በ197 ኪሎ ሜትር እና 4 ሺህ 18 ሄክታር በላይ መሬት መሸፈኑን አንስተዋል።

አረሙን ለመከላከል እና ለማስወገድ የአምስት ዓመት ሰትራቴጂክ እቅድ ተነድፎ እየተሰራ መሆኑን በሪፖርቱ ቀርቧል።

ከህዳር እስከ ጥር ከ 3ሺህ ሄክታር በላይ እምቦጭ አረም ቴክኖሎጂ እና በሰው ጉልበት በመንቀል መቻሉን ዶክተር አያሌው በሪፖርታቸው አቅርበዋል።

ኤጀንሲው ከተመደበለት 45 ሚሊየን ብር ውስጥ እስከአሁን 10 ሚሊየን ብር መጠቀሙም በሪፖርቱ ላይ ቀርቧል።

እንቦጭን ለማስወገድ የፌዴራል እና የክልል መንግስት በቅንጅት ከህብረተሰቡ ጋር በዘመቻ መሰራት እንዳለበት ዶክተር አያሌው ተናግረዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.