Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጅግጅጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው መንግሥት ለክልሎች ልማትና ለመሰረተ ልማት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ይፋዊ ጉብኝት በጅግጅጋ ከተማ አከናውነዋል።

በጉብኝታቸውም ኅብረተሰቡን የበለጠ ለማገልገል ሰፊ የእድሳት ስራ የተከናወነለትን የጅግጅጋ ሼህ ሀሰን ያባሬ ሪፈራል ሆስፒታል ተመልክተዋል።

በተጨማሪም የከተማውን እንቅስቃሴ እና ግንኙነት ለማሳለጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የ18 ኪሎ ሜትር አዲስ የአስፋልት መንገድ ገምግመዋል።

የክልሉን የሕግ ማውጣት እና የዴሞክራሲ እርምጃ ተምሳሌት የሆነውን አዲሱን የክልሉን ምክር ቤት ህንጻም በጉብኝታቸው ተመልክተዋል።

ጉብኝቱ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እየተከናወኑ ያሉትን የዘላቂ ልማት ሥራዎች አፅንኦት የሰጠ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.