Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሸበሌይ ሪዞርት ግንባታን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከ’ገበታ ለትውልድ’ የልማት ቁልፍ ስፍራዎች መካከል አንዱ የሆነውንና በሶማሌ ክልል የሚገኘውን የሸበሌይ ሪዞርት ግንባታ ጎብኝተዋል።

ከጅግጅጋ ከተማ 29 ኪሎ ሜትር ርቀት 385 ሄክታር በሚሸፍን ስፍራ ላይ የሚገነባው ኘሮጀክቱ የጅግጅጋ ከተማ እና አካባቢውን ወደ ግምባር ቀደም የቱሪዝም መዳረሻነት የሚለውጠው የቱሪዝም ስራ አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ስራ ኢትዮጵያ የያዘችውን የዘላቂ ቱሪዝም ስራ እና የኢኮኖሚ እድገት መንገድ አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.