Fana: At a Speed of Life!

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ የልማት ፕሮጀክቶችን የግንባታ ሂደት ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ከትናንት ጀምሮ በክልሉ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ከክልሉ መንግሥት አመራሮች ጋር እየመከረ ነው።

ዛሬ ደግሞ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የአዲሱን የዓባይ ድልድይ የግንባታ ሂደት የተመለከቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው ብሔራዊ ባንክ እያስገነባው ያለውን ሕንጻም አስጀምረዋል።

የሥራ ኀላፊዎቹ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታንም ተመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.