Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው መክፈቻም የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈንታዬ ከበደ ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ የልማት ስራዎች አመርቂ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በጤናው ዘርፍ እና በመንገድ ልማት ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን የምክር ቤቱ አባላት ተዘዋውረው መመልከታቸውንም ጠቅሰዋል።

በክልሉ የአርሶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ የፌዴራል መንግስት በያዘው አቅጣጫ መሰረት የመስኖ ልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም በበጋ ወቅት የማይታረስ የነበረ መሬት በአሁኑ ወቅት በሰብል፣ አትክልትና ፍራፍሬ መሸፈናቸውን ገልጸዋል።

ውጤቱ በቁርጠኝነት ከተሰራ የህዝብን ህይወት መለወጥ እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።

በክልሉ በጤናውም ሆነ በግብርናው ዘርፍ እንዲሁም በመንገድ ልማት ያለው ሽፋን ተመጣጣኝ አለመሆኑንም አንስተው፤ በስራ ደከም ያሉ አካባቢዎች እኩል እንዲለሙ የክልሉ ምክር ቤት ያሉትን ክፍተቶች ገምግሞ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በ6ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረበለትን የአምስተኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ እና አንደኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የቀረበው ቃለ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ቀጣይ አጀንዳዎችን መመልከት ጀምሯል።

በጥላሁን ይልማና ታመነ አረጋ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.