Fana: At a Speed of Life!

ሕዝባዊ ውይይቶችን ለመምራት ከፍተኛ አመራሮች ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና”በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡

ለዚህም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ የሚካሔደውን ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ለመምራት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ወደ ከተማዋ ገብተዋል፡፡

በተመሳሳይ በክልሉ ሚዛን አማን ከተማ የሚካሄደውን የሕዝብ ውይይት ለመምራት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ጌታሁን አብዲሳ ወደ ከተማዋ ገብተዋል፡፡

አመራሮቹ ወደ ቦንጋ እና ሚዛን አማን ከተሞች ሲገቡ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በአካባቢው ነዋሪች አቀባብል ተደርጎላቸዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.