Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡

በውይይት መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው፣ የሐረሪ ክልል ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አሪፍ መሃመድና እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የሃይማኖት አባቶች ፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ሰዎችም ተሳትፈዋል፡፡

አሁን ላይም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተለያዩ ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከነዋሪዎች ጋር መክረዋል፡፡

በሕዝባዊ ውይይቱ ላይ“ሃብት የመፍጠር ጉዟችን ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች” በሚል የመወያያ ፅሑፍ በአቶ አሪፍ መሃመድ ቀርቧል።

በፅሁፉ በተለይም ባለፉት ዓመታት የተጀመረውን ለውጥ ለመቀልበስ በውስጣዊና ውጫዊ ሃይሎች ግፊት ቀውስ ለመፍጠር ተሞክሮ እንደነበርና እሱንም ቀልብሶ ወደፊት የመሄድ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።

የህዝቦችን ትስስር በተመለከተም ብልፅግና ፓርቲ አስተሳሳሪ የሆነና የህዝቦችን ወንድማማችነት የሚያስተሳስር አሰባሳቢ ትርክት ይዞ መምጣቱን አብራርተዋል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

#Ethiopia #Gambella

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.