Fana: At a Speed of Life!

የተፈጥሮ ፀጋዎችን ወደ ልማት በመቀየር ከድህነት ለመውጣት መስራት ይገባል – አቶ ፍቃዱ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ያሉትን የተፈጥሮ ፀጋዎች ወደ ልማት በመቀየር ከድህነት ለመውጣት በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ፍቃዱ ተሰማ ተናገሩ።
 
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ “ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄዷል።
 
በመድረኩ ላይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ÷ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ችግሮቻችንን በመፍታት ለትውልድ የሚተርፍ ሀብት ሊኖረን ይገባል ብለዋል።
 
ያሉትን የተፈጥሮ ፀጋዎች በመጠቀም ከድህነት ለመውጣት ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ገልጸው፤ ለዚህም የመላው ህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
 
ህዝብን ያላሳተፈ ልማት ግቡን አይመታም ያሉት አቶ ፍቃዱ፤ ብልጽግና ፓርቲ ከመጀመሪያ ጉባኤው በኋላ ከህዝብ ጋር የውይይት መድረክ በመፍጠር እንደ ሀገር ያጋጠሙ ጉድለቶች እና ያሉትን ፀጋዎች መለየት እንደተቻለ አብራርተዋል።
 
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበርያ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው፤ የህዝብን ሀሳብ በማድመጥና በመወያየት ለጋራ ችግሮች የጋራ መፍትሄ መፈለግ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
 
ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚገጥሟትን ተግዳሮቶች የመቋቋም አቅም እንዳላትም ጠቅሰዋል።
 
በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)÷ ከዚህ ቀደም በየደረጃው የሚገኘው ህዝብ በርካታ ጥያቄዎች ሲያነሳ እንደነበር አስታውሰዋል።
 
በብልጽግና መርህ እና በህገ መንግስታዊ ስርዓት ለዓመታት ሲንጸባረቅ የቆየውን የህዝብ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ስለማግኘቱም አብራርተዋል።
 
የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ ችግር የዜጎችን በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት የሚገድብ በመሆኑ መንግስት በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል።
 
በስራ እድል ፈጠራ፣ በኑሮ ውድነት፣ በመሰረተ ልማት እና በሌሎችም ጉዳዮች የሚስተዋሉ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች እንዲፈቱ መጠየቁን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
በውይይት ማጠቃለያውም÷ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነትን መቅረፍ እና በሌሎችም ከህዝብ በተነሱ ሀሳቦች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.