Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን መስፋፋትን ተከትሎ የቤት ለቤት የሚደረግ የቆጣሪ የንባብ ስርአትን ለማስቀረት እየተሰራ ነው -የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት -የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኮቪድ 19 ወረርሽኝን መስፋፋትን ተከትሎ የድርጅቶችናንና የቤት ለቤት የሚደረግ የቆጣሪ የንባብ ስርአትን ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ።

የአገልግሎቱ የዲስትሪቢዩዥን ሲስተም ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ከፋናብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷የኮቢድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ በአሁን ወቀት በአንባቢ በኩል በየቤቱ እየዞረ በሚኖር የንባብ ሰራ ንክኪ ሳይኖረው አካላዊ እርቀተን ጠብቆ አንብቦ መሄድ ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል።

ነገር ግን በተገልጋይ በኩል አንባቢ ወደ ቤቱ እንዲመጣበት አይፈልግም የሚሉ ስጋቶች ይኖራሉ በሚል ድርጅቱ አስቀድሞ ትኩረት በመስጠት ይህን መነሻ ያደረገ ስጋትን ለማስቀረት አሰራሩን ለማሻሻል አቅዷል ነው ያሉት።

በአዲሱ አሰራርም የቤት ለቤት ንባብ የሚቀር ሲሆን የድርጅትንና የቤት ለቤት የሚደረግ የቆጣሪ የንባብ ስርአትን ለጊዜው በማስቆም ደንበኞች ባለፉት ስድስት ወራት ሲጠቀሙበት በነበረ የኤሌትሪክ አጠቃቀምን ንባብ ታሳቢ ተደርጎ እንዲከፍሉ ይደረጋል ብለዋል።

በነዚህ ጊዜያት እላፊ የከፈለ ደንበኛ በሚቀጥለው ወር የሚስተካከልለት ሲሆን በተጠቀመበት ልክ ያልከፈለም በተመሳሳይ በቀጣይ ወር እንዲከፍል ይደረጋል ነው ያሉት።

ይህም አሰራር በቀጣይ ወሮች የኮቢድ 19 ወረርሽኝን መስፋፋትን ተከትሎ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም የኢትዮጲያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ደንበኞች በቤታቸው ሆነው በድረገጽ ያለፈ ታሪካቸውን የሚነቡበት እና አገልግሎት የሚያገኙበት የኦላይን አሰራር ለመተገበርም እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በዚህም ለማመልከቻ ፣ ክፍያ ለመክፈልም ሆነ አገልግሎት ለማግኘት የሚቻልበት አሰራር ለመተግበር እየሰራን ነው ያሉት ሃላፊው ÷አሰራርን የማዘመን ስርአት በቀጣይ ለደንበኞች ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

ተቋሙ ወረርሽኙን ተከትሎ የፋይናንስ ጫና እንደተፈጠረበት ጠቁመው÷ በዚህም ቀደም ሲል ከደሞዝ ውጪ በትርፍ ሰአት ይከፍል የነበረውን የሰራተኛ ከፍያ ማስቀረቱን አንስተዋል።

በሌላም በኩል ተቋሙ የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል የደንበኞቹን ጤንነት ለመጠበቅ የተለያዩ አሰራሮቹን በማዘመን ደንበኞቹ በድረገጽ ወይም በአላይን የሚጠቀሙበትን አሰራር ለመዘርጋት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተቋሙ በአሁን ሰዓት ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዬን በላይ ደንበኞች ሲኖሩት ከነዚህ ደንበኞ መካከል በነባሩ ቆጣሪ አገልገሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር ከፍ ያለ መሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህ ቀደም ደንበኞች በተጠቀሙበት ፍጆታ ልክ በየወሩ በባንክ የመክፈል ስርአት መጀመሩ ይታወቃል።

 

በታሪክ አዱኛ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.