Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተመድ ረዳት ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ረዳት ዋና ጸሃፊ እና ከተመድ የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ረዳት ዳይሬክተር እንዲሁም የአፍሪካ ሪጅናል ዳይሬክተር ከሆኑት አሁና ኢዛኩኗ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በወጣቶች እና በሴቶች የስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ መክረዋል።

እንዲሁም በተለያዩ የልማት አጀንዳዎች ዙሪያ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መመክራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.